Meet the Workgroup

አማርኛ • 繁体字 • 简体中文 • ភាសាខ្មែរ • 한국어 • Oromiffa • af-Soomaali • Español • Tagalog • ትግርኛ • Tiếng việt • English

የመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት የስራ ቡድንን (TEW) ለመቀላቀል ያመልክቱ

የመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት የስራ ቡድን (TEW) ለ2023-2024 ክፍት መቀመጫዎች አሉት። ብቁ የሆኑ የማህበረሰብ አባላት እንዲቀላቀሉ እየፈለግን ነው።

የመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት ማዕቀፍ (TEF) እንደ የእኛ አስተናጋጅ ሆነው ማገልገል ይፈልጋሉ? በሲያትል-ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ተጋላጭ ማህበረሰቦችን የሚያገለግሉ ከማህበረሰብ ቡድኖች፣ አውታረ መረቦች ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ሰዎች እንዲያመለክቱ ተጋብዘዋል።

አመልካቹን መደገፍ ይፈልጋሉ? ከመጓጓዣ ፍትሃዊ እኩልነት የስራ ቡድን (TEW) እጩዎች ጋር የተገናኙ ድርጅቶች የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይችላሉ።


የትርጉም አገልግሎቶች

የትርጉም አገልግሎት ይፈልጋሉ? ማመልከቻዎችን ወይም የድጋፍ ደብዳቤዎችን ለማስገባት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ግለሰቦች ወይም ቡድኖች:

የአሁን የስራ ቡድን አባላት

ዮርዳኖስ ተፈሪ፣ የስራ ቡድን ተባባሪ ሊቀመንበር

ዮርዳኖስ ተፈሪ አንድ የኢዲከቨሪ (eDiscovery) ጠበቃ ናቸው። እሷ በሕግ እና በፎርቹን 100 (Fortune 100) ኩባንያዎች ከ17 ዓመታት በላይ ልምድ አላት። ዮርዳኖስ በኤርትራ ኮሚኒቲ ማዕከል ቦርድ ላይ ማገልገል ስትጀምር ለታላቁ የመድብለ ባህላዊ ማህበረሰብ ጥምረት (Multicultural Community Coalition) ስራ ተዋውቃለች። ዛሬ እሷ ዋና ዳይሬክተር ሆና ታገለግላለች። ዮርዳኖስ በፍትሃዊ እኩልነት የልማት ተነሳሽነት (EDI) የቦርድ አማካሪ እና የዕድል ማህበረሰቦች (COO) የአስተዳደር ቦርድ ላይ ታገለግላለች።

ዩ አን ዩን (Yu Ann Youn)፣ የስራ ቡድን ተባባሪ ሊቀመንበር

ዩ-አን ዩን በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ የሮቢንሰን የወጣት ምሁራን ማዕከል በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪዋን እየሰራች ያለች ተማሪ ነች። በተገነባው የአካባቢ ኢንደስትሪ ውስጥ የዘር ፍትሃዊነትን እና ብዝሃነትን መገንባት ትወዳለች እና በከተማ ፕላን እና ልማት ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር የበለጠ ግንኙነት ለመፍጠር ንቁ ተሟጋች ነች። በትራንስፖርት እቅድ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ጥቁሮች፣ ተወላጆች እና ነጭ ያልሆኑ (BIPOC) ማህበረሰቦች እና ወጣቶችን ድምጽ ለማምጣት የትራንስፖርት ፍትሃዊነት የስራ ቡድንን ተቀላቀለች።

Rizwan Rizwi፣ ተባባሪ ሊቀመንበር Emeritus

ሪዝዋን (Rizwan) የሳር ሀብት አስተዳደር (SAR Wealth Management) ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ነው። ተወልዶ ያደገው በእንግሊዝ አገር ኒውካስል አፖን ታይን ኢንግላንድ በተባለ ቦታ ሲሆን ከኒውካስል ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት በቢኤ በክብር እንዲሁም ቀጥሎ ብቢዝነስ አድሚኒስረሽን በኤምኤ ተመርቋል። በኢንቨስትመንት ኢንዱስትሪ ውስጥ ሰፊ ልምድ ያለው እና በSMITH BARNEY Citigroup (አሁን የሞርጋን ስታንሊ አካል) የፍትሃዊነት ፖርትፎሊዮን በማስተዳደር ለተወሰኑ አመታት አሳልፏል።

እ.ኤ.አ. በ2012፣ ሪዝዋን የሙስሊም ቤቶች አገልግሎት (MHS) ዋና ዳይሬክተር ሆነ፣ በ2018 በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ከ1,100 በላይ ሰዎችን በዋነኛነት ቤት አልባ ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን ቤት እንዲያገኙ ረድተዋል። እሱ በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ካሉ ወይም በታሪክ ብዙም ያልተወከሉ በፖሊሲ ንድፉ ችላ ከሚባሉ ቡድኖች ቢመጣም በሲያትል ዲፓርትመንት ትራንስፖርት የፍትሃዊነት የስራ ቡድን የተቀላቀለው ሰዎች በትራንስፖርት ውሳኔውች አስተያየት እንዲኖራቸው ለማድረግ ።

ስቲቨን ሰውየር (Sawyer Sawyer)፣ ተባባሪ ሊቀመንበር Emeritus

ጳጳስ ስቲቨን አር. ሳውየር (Steven R. Sawyer) የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የማህበረሰብ መሪ፣ ስራ ፈጣሪ፣ እና የብሄራዊ ሀይማኖት ኣቅኚ በቢዝነስ አስተዳደር ቢኤ እና በድርጅታዊ አስተዳደር ከፍተኛ ትኩረት ያለው እንዲሁም ማስትሬት ዲግሪ በመለኮታዊ ትምህርት እና በአለም አቀፍ ልማት እና ፍትህ ከማልትኖማህ ዩኒቨርሲቲ በፖርትላንድ፣ ኦሬጎን። በአሁኑ ጊዜ፣ ስቲቨን የ POCAAN ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ፣ ቀደም ሲል ነጭ ያልሆኑ ሰዎች ተቃርኖ አውታረ መረብ ኤድስ በመባል የሚታወቀው፣ ከ1987 ጀምሮ በሲያትል ውስጥ የተገለሉ ማህበረሰቦችን የሚያገለግል የመድብለ ባህላዊ ማህበራዊ አገልግሎት ኤጀንሲ ይሰራል። ኤጀንሲው የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀምን፣ እስራትን፣ ቤት እጦትን፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን፣ ዘረኝነትን፣ ሴሰኝነትን፣ ግብረ ሰዶማዊነትን፣ እና ሌሎች ኣግላይ የሆኑ ልዩነቶችን የሚመለከቱ ፕሮግራሞችን ለመፍታት መደገፍ፣ ማስተማር፣ እና ማንቀሳቀስ ይፈልጋል። የእሱ መፈክር ከድርጅቱ ጋር ተጋርቷል፡ "ጤናን ማስተዋወቅ፣ ማህበረሰብን ማሰባሰብ፣ እና ህይወትን መለወጥ።

አን ሁይንህ (An Huynh)

አን ሁይንህ በሲያትል ቻይናታውን አለም አቀፍ ዲስትሪክት የጥበቃ እና ልማት ባለስልጣን (SCIDpda) የህዝብ ቦታ እና ማህበረሰብ አስተባባሪ ናት። በቻይናታውን ኢንተርናሽናል ዲስትሪክት ውስጥ ከአካባቢው ንግዶች፣ ነዋሪዎች፣ እና የንብረት ባለቤቶች እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ዲፓርትሜንቶች፣ የገንዘብ ሰጪዎች፣ እና የንድፍ ኩባንያዎች ጋር በመገናኘት(በተለያዩ ዲዛይኖች እንደ ህዝባዊ ስነጥበብ፣ የፓርክ ንድፍ፣ እና የእግረኛ መንገድን ማነቃቃት ፕሮጀክቶች ስምምነት ላይ ለመድረስ የማህበረሰብ ተሳትፎን እና የሕዝብ ቦታዎችን ፕሮጄክቶች ተደራሽነትን ታመቻቻለች። በቻይናታውን አለምአቀፍ ዲስትሪክት ውስጥ የሚኖሩ 72% ቤተሰቦች ከእንግሊዝኛ ዉጭ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ እና 19.1% አዛውንት በሚሆኑበት በቻይናታውን አለምአቀፍ ዲስትሪክት ውስጥ የሚኖሩትን ሁለቱም ብዙውን ጊዜ ከትራንስፖርት ፍትሃዊነት ንግግሮች ውጭ የሆኑትን ሰዎች ልምድ ለማሳደግ አን (An) የትራንስፖርት እኩልነት የስራ ቡድንን (TEW) ተቀላቃለች።

አሚር ኑር ሶልኪን (Amir Noir Soulkin)

አሚር ኑር ሶልኪን የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ኣገልግሎቶች (EACS) የግንኙነቶች እና ልማት ዳይሬክተር ነው፣ ከተመሰረተ 21 አመት የሆነው በጥቁር የሚመራ እና (ለትርፍ ያልተቋቋመ በምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰቦች የቆመ እና እነርሱን የሚያገለግል ነው። እሱ ለድርጅቱ የመጀመሪያ ደረጃ የግንኙነት ሰው ሲሆን የድርጅቱን የገንዘብ ማሰባሰብ እና የልማት ክፍልን ይቆጣጠራል። የምስራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ አገልግሎቶች (EACS) ሲያትል በኒው ሆሊ አካባቢ ይገኛል፣ በጣም ብዙ የBIPOC ማህበረሰብ የያዘ ከ350 በላይ ወጣቶችን በባህላዊ ስር በሰደደ ከቅድመ-ትምህርት እስከ 12ኛ ክፍል ድህረ ትምህርት፣ የበጋ፣ እና ጣልቃ ገብነት እና የተለያዩ የምክሮች ፕሮግራሞች ለወጣቶች ይሄዉም የምስራቅ አፍሪካ ስደተኛ እና ተፈናቃዮች ቤተሰቦች ድምጻቸውን ከፍ ኣድርገው እንዲያሰሙ የሚያበረታታ ነው።

አሚር ከፑጀት ሳውንድ ሳጅ ኮሚኒቲ አመራር ኢንስቲትዩት (Puget Sound Sage's Community Leadership Institute) የተመረቀ ሲሆን በህዝብ ተንቀሳቃሽነት እና ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተመጣጣኝ እና ፍትሃዊ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ማግኘት መካከል ያለውን ትስስር እና ይህም ሁሉንም የህይወት ገፅታዎችን የሚያገናኝ ትልቅ ግንዛቤን አግኝቷል። ጥቁር መጤዎች ብዙውን ግዜ በቋንቋ እና/ወይም በሌላ እንቅፋቶች ምክንያት ከፖሊሲ ንግግሮች ውጭ ይሆናሉ፣ ይኸውም በነቃ የዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ቅርጽ ያለው ማህበረሰብ ዉስጥ ለሚኖሩ የተገለሉ ማህበረሰቦች በጣም አደገኛ ነው። አሚር በትራንስፖርት ፍትሃዊነት የስራ ቡድን ውስጥ በማገልገል የምስራቅ አፍሪካን ስደተኛ እና ተፈናቃዮች ማህበረሰቦችን በመወከል ጠቃሚ እና ውጤታማ የሆነ የፍትሃዊነት ስራ መሳተፍ እንደሚችል ተሰምቶት ነበር፡ “ውክልና ኣስፈላጊ ነው። የጥቁሮች፣ ተወላጆች እና ነጭ ያልሆኑ (BIPOC) አንድነት ዋጋ ኣለው። የጥቁር ሕይወቶች ዋጋ አላቸው የጥቁር ድምፆች አስፈላጊ ዋጋ አላቸው። የጥቁር ፍላጎቶት ዋጋ አላቸው። የጥቁር ኢኮኖሚ ዋጋ አላቸው። የጥቁር የህይወት ጥራት አስፈላጊ ነው።"

ካሪያ ዎንግ (Karia Wong)

ካሪያ ዎንግ ከ 1998 ጀምሮ ስደተኞችን በማገልገል ላይ ትገኛለች ፣ በመጀመሪያ በጎ ፈቃደኝነት እና አሁን የቻይናዊያን የመረጃ እና የአገልግሎት ማእከል (CISC)፣ የቤተሰብ መገልገያ ማእከል አስተባባሪ። ከ20+ ዓመታት ስደተኞችን ስትደግፍ፣ ካሪያ የትራንስፖርት ኢ-ፍትሃዊነት ለስደተኞች በሲያትል ውስጥ በአዲሱ ህይወታቸው እንዲበለጽጉ እንቅፋት እንደሚሆን አይታለች። ሁሉም ሰው የትውልድ አገሩ፣ ቋንቋው፣ ዳራ እና አካላዊ/አእምሯዊ አቅሙ ምንም ይሁን ምን፣ ሁሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተመጣጣኝ፣ ተደራሽ እና ለአካባቢ ዘላቂነት ያለው የመጓጓዣ አማራጮች ተመሳሳይ መዳረሻ ሊኖረው ይገባል ብላ ታምናለች።

የቀድሞ የትራንስፖርት እኩልነት የስራ ቡድን (TEW) አባላት

  • ሲሳር ጋርሲያ (Cesar Garcia)
  • ኤላኒ ካይስ (Ellany Kayce)
  • Khatami Chau
  • Kiana Parker
  • Kristina Pearson
  • Chris Rhoades
  • Christina Thomas
  • Phyllis Porter
  • Micah Lusignan
  • Julia Jannon-Shields
  • ሶኩንቲያ ኦክ፣ (የጎረቤቶች መምሪያ (DON)፣ የማህበረሰብ ግንኙነት)
  • አናሊያ በርቶኒ፣ (የጎረቤቶች መምሪያ (DON)፣ የማህበረሰብ ግንኙነት)

Transportation

Greg Spotts, Director
Address: 700 5th Ave, Suite 3800, Seattle, WA, 98104
Mailing Address: PO Box 34996, Seattle, WA, 98124-4996
Phone: (206) 684-7623
684-Road@seattle.gov

Newsletter Updates

Subscribe

Sign up for the latest updates from Transportation

The Seattle Department of Transportation (SDOT) is on a mission to deliver a transportation system that provides safe and affordable access to places and opportunities for everyone as we work to achieve our vision of Seattle as a thriving, equitable community powered by dependable transportation.