Rainier Ave S አውቶቡስ-ብቻ መስመር
አማርኛ • اَلْعَرَبِيَّةُ • 繁体字 • af-Soomaali • Español • Tagalog • ትግርኛ • Tiếng việt • English • 简体中文 • 한국어 • 日本語
መስከረም 19 ቀን 2022 ተዘምኗል
የሕዝብ መጓጓዣ አስተማማኝነትን እና የጉዞ ጊዜን ማሻሻል
አሁን ምን እየሆነ ነው ያለው?
Join the public meeting online using this link:
https://seattle.webex.com/seattle/j.php?MTID=mf00ad4b5c8710b01264144f9742c9612
Webinar password: ZRqnvrEE822 (97768733 from phones)
Webinar number: 2497 593 1882
Join the public meeting by phone:
+1 (206) 207-1700 United States Toll (Seattle)
+1 (408) 418-9388 United States Toll
Access code: 249 759 31882
- መኪናዎችን እና የጭነት መኪናዎችን የሚነዱ ሰዎች "አውቶቡስ-ብቻ" በተጻፈባቸው እና ምልክት በተደረገባቸው መስመሮች መጓዝ አይችሉም። ቀይ ቀለም የተቀቡ መስመሮች ለአውቶቡሶች ብቻ በቀን ለ24 ሰአታት እና በሳምንት ለ7 ቀናት የተገደቡ ናቸው።
- የሚያሽከረክሩ ሰዎች የአውቶቡስ ብቻ መስመር ውስጥ ወደ ሰፈር መንገዶች እና መስቀለኛ መገናኛዎች ላይ ለመታጠፍ መግባት ይችላሉ
- ብስክሌት የሚጋልቡ ሰዎች የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን መጠቀም ይችላሉ
- የአደጋ ምላሽ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ለአደጋ ምላሽ ሲሰጡ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን መጠቀም ይችላሉ
- የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ብቻ የ "አውቶቡስ-ብቻ" ምልክት የተደረገባቸው መስመሮችን እንዲጠቀሙ ተፈቅዶላቸዋል። ይህ የትምህርት ቤት አውቶቡሶችን፣ የሚጋሯቸው መለስተኛ አውቶቡሶችን፣ የስራ ማመላለሻዎችን፣ የሞተር ብስክሌቶችን፣ የሚጋሯቸው መኪናዎችን ወይም የኮንትራት አውቶብሶችን አያካትትም።
ስለሕዝብ ማመላለሻ መስመሮች፣ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእኛን የሕዝብ ማመላለሻ መስመር ድረ-ገጽ ይጎብኙ።
የፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ
አውቶቡሶችን ከሌሎች ተሽከርካሪዎች በመለየት የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ ይረዳሉ። የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች የአውቶቡስ ጉዞ ጊዜን በተለይም ትራፊክ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ፣ ከመጨናነቅ ጋር የተያያዙ መዘግየቶችን ይቀንሳሉ። ግባችን በሲያትል ውስጥ ለሚኖሩ፣ ለሚሰሩ እና ለሚጎበኙ ሰዎች ሁሉ የሕዝብ መጓጓዣን ተደራሽ፣ ምቹ እና አስተማማኝ የመጓጓዣ ምርጫ ማድረግ ነው። ለዚህ ግብ እየሠራንበት ያለንበት አንዱ መንገድ የአውቶብስ-ብቻ አውታረ መረብ መስመሮቻችንን በማስፋፋት ብዙ ሰዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማንቀሳቀስ የሚችል የበለጠ አስተማማኝ እና ውጤታማ የሆነ የሕዝብ ማጓጓዣ ስርአት በመፍጠር ነው።
በRainier Valley ውስጥ የሕዝብ ማጓጓዥ አስተማማኝነትን ለማሻሻል ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ጋር በመተባበር እየሰራን ነው። መስመር 7 የሲያትል እጅግ በጣም ከተጨናነቀ የአውቶቡስ መስመሮች አንዱ ሲሆን በቀን 8,000 ተሳፋሪዎችን (ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት 11,200 ተሳፋሪዎች) ያገለግላል። መስመር 7 አውቶቡሶች በየ10 ደቂቃው ወይም ከዚያ ቀድመው እንዲመጡ ታቅዶ እያለ፣ አውቶቡሶች ብዙ ጊዜ የሚዘገዩት በ Rainier Ave S ላይ ባለው የትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ነው። በዚህ አስፈላጊ ኮሪደር ላይ የመጓጓዣ አስተማማኝነትን ለማሻሻል እንዲረዳን፣ በRainier Ave S ላይ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን እየጨመርን ነው። ይህ ሥራ በሁለት ደረጃዎች ይከናወናል:
ደረጃ 1 (ነሐሴ 2022 ተጠናቅቋል) በS Alaska St እና S Walden St መካከል ወደ ሰሜን እቅጣጫ የሚሄድ አውቶቡስ-ብቻ መስመር፣ እና በደቡብ አቅጣጫ ያለው አውቶቡስ-ብቻ መስመር በS Oregon St እና S Edmunds St መካከል ሠርተናል። አንድ የጉዞ መስመር ወደ አዲሱ አውቶቡስ-ብቻ መስመር ተቀይሯል እና ምንም ነባር የጎዳና ላይ ማቆሚያ አልተወገደም። በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ የትራፊክ ዘይቤዎች እንዴት እንደሚለወጡ በተሻለ ለመረዳት በራኒየር ጎዳና ደቡብ እና ሌሎች በአቅራቢያው ባሉ መንገዶች ላይ የትራፊክ መጠኖችን እየተከታተልን ነው። ከዚያ በምንማረው መሰረት፣ ትራፊክን ለመቆጣጠር እና ለማረጋጋት ወደፊት ማስተካከያዎችን ማድረግ ወይም ለመቆጣጠር የሚረዱ ሌሎች ለውጦችን መተግበር እንችላለን።
ደረጃ 2 (2022 ማስታወቁን ማዳረስ) Rainier Ave S ላይ ወደ ሰሜን አቅጣጫ የአውቶቡስ ብቻ መስመሮች ማስፋፋትን ጨምሮ፣ የሕዝብ ማመላለሻ አስተማማኝነትን እና የጉዞ ጊዜዎችን የበለጠ ለማሻሻል ተጨማሪ ለውጦችን እየገመገምን ነው። በአሁኑ ወቅት የሰሜን አቅጣጫ አውቶቡስ ብቻ መስመርን ከRainier Ave S ወደ S Grand St አራዝሞ የሚዘረጋበትን አማራጮች እየገመገምን ነው። ይህ ለውጥ አውቶብስ የሚሳፈሩትን ሰዎች ጠዋት ትራፊክ በተጨናነቀበት ሰዓቶች 5 ደቂቃዎችን ያድንላቸዋል ብለን እንገምታለን።
ሁለት አማራጮችን እየገመገምን ነው:
- በS Walden St ወደ S Grand St መካከል ቀጣይነት ያለው ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሚሄድ የአውቶቡስ-ብቻ መስመር፣ አንድ የአጠቃላይ ጉዞ መስመር፣ እና ባለሁለት መንገድ የመሀል ማዞሪያ መስመር
- 2 ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሚጓዙ የጉዞ መስመሮችን የሚያቆይ በS Walden St እና S Grand St መካከል ቀጣይነት ያለው የሰሜን አውቶቡስ-ብቻ መስመር እና በS Grand St ወደ S College St መካከል ያለውን ባለሁለት መንገድ መሃል መታጠፊያ መስመር የሚያስወግድ
ጥቅማጥቅሞችን እና ሌሎች የታሰቡ ጉዳዮችን ጨምሮ፣ ስለ ሁለቱ አማራጮች ተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ቀርቧል።
በS Walden St ወደ S Grand St መካከል ያሉ የተለመዱ ሁኔታዎች
- በሁለቱም አቅጣጫዎች ሁለት አጠቃላይ የትራፊክ መስመሮች
- ባለ ሁለት መንገድ የማዞሪያ መስመር
ወደ ሰሜን ስታይ ያለ ምስል።
አማራጭ 1
- ቀጣይ ወደ ሰሜን የሚሄድ አውቶቡስ-ብቻ መስመር ከS Walden St እስከ S Grand St ድረስ ያለው
- አንድ ወደ ሰሜን አቅጣጫ የሚሄድ አጠቃላይ የጉዞ መስመር
- ባለ ሁለት መንገድ የመሃል መዞሪያ መስመርን ይቆያል
ጥቅሞች:
- የመጓጓዣ አስተማማኝነትን እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሻገሪያዎችን ለማራመድ በS Grand St አዲስ የትራፊክ ምልክት
- ሁኔታዎች ከወትሮው የበለጠ በሚጨናነቁበት ወቅት በግምት ወደ 5 ደቂቃዎች የሚጠጋ የመጓጓዣ ጊዜን እንደሚቆጥብ ይገመታል
- አውቶቡሱን መሳፈር ይበልጥ አስተማማኝ እና የሚስብ የመጓጓዣ አማራጭ ያደርገዋል
- በከተማ የአየር ንብረት እና የፍትሃዊ እኩልነት ግቦች ላይ እድገት ያደርጋል
ሊሆኑ የሚችሉ:
- በአጎራባች መንገዶች ላይ የትራፊክ አቅጣጫ መለወጥን ሊያስከትል ይችላል
- በጥዋቱ ከፍተኛ የትረፊክ ሰዓታት ወቅት በRainier Ave S ወደ ሰሜን አቅጣጫ ለሚነዱ ሰዎች የጉዞ ጊዜ በ9 ደቂቃዎች ሊጨምር ይችላል
- አውቶቡስን ለመውሰድ እንቅፋቶችን ለመፍታት ተጨማሪ መዋዕለ ንዋዮች ያስፈልጉ ይሆናል
ወደ ሰሜን ስታይ ያለ ምስል።
አማራጭ 2
- ቀጣይ ወደ ሰሜን የሚሄድ አውቶቡስ-ብቻ መስመር ከS Walden St እስከ S Grand St ድረስ ያለው
- በኤስ ግራንድ ሴንት እስከ ኤስ ኮሌጅ ሴንት መካከል፣ ሁለት ወደ ሰሜን የሚሄዱ የጉዞ መስመሮችን ይጠብቁ እና ባለሁለት መንገድ መሃል መታጠፊያ መስመርን ያስወግዱ
ጥቅሞች:
- የመተላለፊያ አስተማማኝነትን እና አስተማማኝ መሻገሪያዎችን ለማራመድ በS Grand St እና S College St ላይ ሁለት አዳዲስ የትራፊክ ምልክቶችን ይጨምራል። በS College St ያለ አዲስ የትራፊክ ምልክት የተጠበቀ የግራ መታጠፊያዎችን ያቀርባል።
- ሁኔታዎች ከወትሮው የበለጠ በሚጨናነቁበት ወቅት በግምት ወደ 5 ደቂቃዎች የሚጠጋ የመጓጓዣ ጊዜን እንደሚቆጥብ ይገመታል
- ለI-90 መዳረሻ ሁለት የሰሜን አቅጣጫ የጉዞ መስመሮችን ያቆያል
- አውቶቡሱን መሳፈር ይበልጥ አስተማማኝ እና የሚስብ የመጓጓዣ አማራጭ ያደርገዋል
- በከተማ የአየር ንብረት እና የፍትሃዊ እኩልነት ግቦች ላይ እድገት ያደርጋል
ሊሆኑ የሚችሉ:
- በS Walker St እና S Holgate St መካከል የግራ መታጠፊያዎችን ይገድባል
- ሁሉንም የጉዞ መስመር ስፋቶችን ማስተካከል ያስፈልገዋል
- በአጎራባች መንገዶች ላይ የትራፊክ አቅጣጫ መለወጥን ሊያስከትል ይችላል
- በRainier Ave S ወደ ሰሜን አቅጣጫ ብኩል ለሚነዱ ሰዎች በጠዋቱ የከፍተኛ ትራፊክ ሰዓቶች የጉዞ ጊዜዎች በ 5 ደቂቃዎች ሊጨምር ይችላል
- አውቶቡስን ለመውሰድ እንቅፋቶችን ለመፍታት ተጨማሪ መዋዕለ ንዋዮች ያስፈልጉ ይሆናል
በS Grand St ወደ S College St የመንገድ ንድፍ (ወደ ሰሜን ሲታይ)
በS College St ወደ S Walden St የመንገድ ንድፍ (ወደ ሰሜን ሲታይ)
በእነዚህ አማራጮች ላይ የእርስዎን አስተያየት እንፈልጋለን። እባክዎን የዳሰሳ ጥናታችንን ይውሰዱ!
የፕሮጀክት አካባቢ ካርታ:
የፕሮጀክት ዳራ:
Rainier Ave S ሰዎችን በከተማው ውስጥ ካሉ ንግዶች እና የባህላዊ ማዕከሎች ጋር የሚያገናኝ ዋና የደም ቧንቧ መንገድ ነው። እንዲሁም እቃዎችን ወደ መድረሻቸው የሚያንቀሳቅሱ ሰዎችን የሚያገናኝ አነስተኛ የእቃ መጫኛ ኮሪደር ነው። Rainier Ave S የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ 4፣ 7፣ 9፣ 48፣ 50 እና 106 መስመሮችን የሚያገለግል አስፈላጊ የሕዝብ ማጓጓዣ ኮሪደር ነው። መስመር 7 አውቶብስ በማደግ ላይ ያለውን የሬኒየር ሸለቆን እና በተለምዶ ውክልና ያልተሰጣቸው እና አገልግሎት የማይሰጡ ማህበረሰቦችን በቀጥታ ያገለግላል። በሬኒየር ቫሊ ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በየቀኑ እንደ ትምህርት ቤቶች፣ የግሮሰሪ መደብሮች፣ ስራዎች እና የማህበረሰብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ያሉ የአካባቢ አገልግሎቶችን ለማግኘት በመስመር 7ቱ አውቶቡስ ላይ ጥገኛ ናቸው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሰዎች በመስመር 7ቱ ላይ መተማመናቸውን ቀጥለዋል እና የአውቶቡስ መስመሩ ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት አንዳንድ ከፍተኛ የተሳፋሪነት ቁጥርን ጠብቆ ቆይቷል።
በወረርሽኙ ወቅት መስመር 7 አንዱ ከፍተኛ የሕዝብ መጓጓዣ ተሳፋሪ ነበረው። በ 2020 የበልግ ወቅት፣ መስመር 7 ከኮቪድ በፊት 60% የነበረውን ተሳፋሪነትን ይዞ ቆይቷል።
ይህ ፕሮጀክት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ ሁሉ የሕዝብ መጓጓዣ ተሳፋሪነት ከፍተኛ በሆነበት መስመር የሕዝብ መጓጓዣ አስተማማኝነትን እና የጉዞ ጊዜን ለማሻሻል እንደ ቅርብ ጊዜ አጋጣሚ ሆኖ ተመርጧል። አሁን እነዚህን መዋዕለ ንዋዮችን በማድረግ፣ ከወረርሽኙ ማገገማችንን ስንቀጥል የሕዝብ መጓጓዣ ለሰዎች አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የማመላለሻ አማራጭ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል።
የRainier Ave S የመጓጓዣ መስመር ፕሮጀክት በሬኒየር ሸለቆ ውስጥ የሕዝብ መጓጓዣ አስተማማኝነትን ለማሻሻል ከቀደምት የማዳረስ እና የእቅድ ጥረቶች ይገነባል። በማመላለሻ ፍላጎቶች እና እንደ RapidRide R Line ፕሮጀክት አካል በRainier Ave S ላይ ቅድሚያ ሊሰጣቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች የሲያትል የማመላለሻ መምሪያ (SDOT) እና ኪንግ ካውንቲ ሜትሮ በ2017-2018 እና እንደገና በ2019-2020 የማህበረሰብ ግብአቶችን መሰብሰብ አከናውነዋል። በዚያ የማዳረስ በኩል የሚከተሉትን ሰምተናል:
- ሰዎች በRainier Ave S (ወደ መሃል ከተማ ከመጓዝ ይልቅ) መድረሻዎች እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለመድረስ አስተማማኝ የሕዝብ መጓጓዣ ይፈልጋሉ
- ያነሰ ጊዜ የሚወስዱ እና ከሌላ የሕዝብ መጓጓዣ ጋር ከሚያገናኙ ለሕዝብ መጓጓዣ ጉዞዎች ድጋፍ
- ወደ አውቶቡስ ፌርማታዎች (በተለይ በአውቶቡስ ፌርማታዎች አቅራቢያ ባሉ ማቋረጫዎች) ለሚሄዱ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ተደራሽነት
- በቻይናታውን-ዓለም አቀፋዊ ወረዳ እና በMt Baker Link Light Rail Station መካከል ላለ የአውቶቡስ-ብቻ መስመር ድጋፍ
- ብዙ ሰዎች የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን ለመጨመር የመንገድ ላይ የመኪና ማቆምን ለማስወገድ የቀረበውን ሀሳብ ይደግፋሉ፣ ነገር ግን በአነስተኛ ንግዶች ላይ ሊደርሱ ስለሚችሉ ተጽዕኖዎች ስጋቶች አሉ
የፕሮጀክት ጥቅሞች
- እንደ መስመር 7፣ 48 እና 106 ያሉ ከፍተኛ ተሳፋሪነት ያሉባቸውን ተደጋጋሚ መንገዶችን ጨምሮ፣ በRainier Ave S ላይ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን መጨመር እና ማስፋፋት በRainier Ave S ላይ የሕዝብ መጓጓዣ አስተማማኝነትን ያሻሽላል
- ከወረርሽኙ በጋራ ስናገግም እና እንደገና ስንገነባ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮችን አሁን መጨመር የሕዝብ መጓጓዣ የህይወት መስመር ሆኖ እንዲቀጥል እና የሬኒየር ቫሊ ማህበረሰብን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ያስችላል
- ከነባር የሕዝብ መጓጓዣ ማዕከሎች በተጨማሪ እንደ Mt. Baker Light Rail Station እና the McClellan St Metro Transit Station ያሉት፣ የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች በአውቶቡሱ ላይ ያሉ ሰዎችን በ2023 ከሚከፈተው አዲሱ Judkins Park Light Rail Station ጋር በተቀላጠፈ መንገድ ያገናኛሉ
- አንድ ወደ ሰሜን የሚሄድ በየ3.5 ደቂቃው ከሚመጣው አውቶቡስ ጋር፣ የRainier Ave S በ AM ጠዋት በከፍተኛ የትራፊክ ጊዜ በጣም ተደጋጋሚ የአውቶቡስ አገልግሎትን ይሰጣል። የአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች የበለጡ ሰዎችን ወደሚሄዱበት ቦታ በሰዓቱ እንዲደርሱ እና የበለጠ ወጥ የሆነ የጉዞ ጊዜ እንዲለማመዱ ይረዳቸዋል። የአውቶቡስ ብቻ መስመር ከተዘረጋ በኋላ በአማካይ የጠዋት ጉዞ፣ በአውቶቡስ ላይ ያሉ ሰዎች 2 ደቂቃ መቆጠብ ይችላሉ። በጣም በተጨናነቀ የጠዋት ጉዞዎች፣ በአውቶቡስ ላይ ያሉ ሰዎች በአውቶቡስ ብቻ መስመር 6 ደቂቃ መቆጠብ ይችላሉ።
- የደረጃ 1 ፕሮጀክት መጠናቀቅ በS Alaska St እና በS Walden St መካከል በአውቶቡስ ወደ ሰሜን የሚጓዙትን ሰዎች ከ1 ደቂቃ በላይ ይቆጥብላቸዋል ብለን እንጠብቃለን። የትራፊክ መጠኑ ከፍ ባለበት እና መጨናነቅ ሁል ጊዜ የሚበዛበት የአውቶቡስ-ብቻ መስመር ወደ ሰሜን ወደ I-90 አስፋፍቶ በመዘርጋት የበለጠ የሕዝብ ጉዞ ጊዜን ቆጣቢ እንደሚሆን እንገምታለን።
ስለ Rainier Ave S አውቶቡስ-ብቻ መስመሮች የበለጠ ይወቁ
የሕዝብ መጓጓዣ መስመሮች ከተገነቡ በኋላ አውቶቡሶች ምን ያህል ጊዜ ይቆጥባሉ?
የደረጃ 1 ፕሮጀክት መጠናቀቅ በS Alaska St እና በS Walden St መካከል ወደ ሰሜን ለሚጓዙ አውቶቡስ ሰዎች ከ1 ደቂቃ በላይ ይቆጥባል ብለን እንጠብቃለን። የአውቶቡስ-ብቻ መስመር ወደ ሰሜን ወደ I-90 ከተዘረጋ የትራፊክ መጠኑ ከፍ ባለበት እና መጨናነቅ ሁል ጊዜ የሚበዛበት ከሆነ የበለጠ ጊዜ ቆጣቢ እንደሚሆን እንጠብቃለን። እንደ ደረጃ 2 ፕሮጀክት አካል የእነዚህን ጊዜ የመቆጠብ አቅም መገምገማችንን እንቀጥላለን።
ለምንድነው አሁን የአውቶቡስ ብቻ መስመሮችን የሚታክሉት?
ይህ ፕሮጀክት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ ሁሉ የሕዝብ መጓጓዣ ተሳፋሪነት ከፍተኛ በሆነበት መስመር የሕዝብ መጓጓዣ አስተማማኝነትን እና የጉዞ ጊዜን ለማሻሻል እንደ ቅርብ ጊዜ አጋጣሚ ሆኖ ተመርጧል። አሁን እነዚህን መዋዕለ ንዋዮችን በማድረግ፣ ከወረርሽኙ ማገገማችንን ስንቀጥል የሕዝብ መጓጓዣ ለሰዎች አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የማመላለሻ አማራጭ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል።
የመኪና ማቆሚያ ተጽእኖዎች ሊኖሩ ይችላሉ?
ለደረጃ 1 ኘሮጀክቱ ምንም ነባር የመንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ አይወገድም። የፕሮጀክት እቅድ እና ንድፍ እየቀጠለ ሲሄድ ከደረጃ 2 ፕሮጀክቱ የሆኑ ማንኛቸውም በመንገድ ላይ የመኪና ማቆሚያ ተፅእኖዎች ይወሰናል።
ወደ ንግዶች እና/ወይም የመኖሪያ ቤቶች መዳረሻ ይቀየራል?
የለም፣ በRainier Ave S ላይ የንግድ ድርጅቶች እና/ወይም የመኖሪያ ቤቶች መዳረሻ በደርጃ 1 ፕሮጀክት አይቀየርም። የሚያሽከረክሩት ሰዎች አሁንም ወደ መስቀለኛ መገናኛዎች ወይም ወደ ንግዶች/መኖሪያ ቤቶች ለመዞር የአውቶቡስ-ብቻ መስመር መግባት ይችላሉ። ከደረጃ 2 ፕሮጀክት የሚመጡ ማናቸውም የመዳረሻ ለውጦች ገና አልተወሰኑም።
የቤት መኪናዎች እና የጭነት መኪናዎችን በሚያሽከረክሩት ሰዎች ላይ ሊያመጣ የሚችል የተጽእኖች አቅም ምንድነው?
የደረጃ 1 ፕሮጀክት ከተገነባ በኋላ የቤት መኪናዎች እና የጭነት መኪናዎችን በሚነዱ ሰዎች ጉልህ የሆነ የጉዞ ጊዜ ተጽእኖችን አንጠብቅም። እንደ የደረጃ 2 ፕሮጀክት አካል፣ የቤት መኪናዎች እና የጭነት መኪናዎችን በሚያሽከረክሩ ሰዎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉትን ተፅዕኖዎች ማጥናታችንን በመቀጠል እነዚያን ተፅእኖዎች ለመቆጣጠር ወይም ለመቀነስ ስልቶችን ለመለየት እንሰራለን።
በአጎራባች ሰፈሮች ውስጥ የሚያቋርጡ ትራፊክን እንዴት እያስተናገዱ ነው?
በመንገዶች መጨናነቅን ለማስወገድ አንዳንድ የሚያሽከረክሩ ሰዎች በመኖሪያ ሰፈሮች ውስጥ አማራጭ መንገዶችን መውሰድ እንደሚመርጡ እንረዳለን። አሁን ካለው የትራፊክ መጠኖች አንጻር፣ ከደረጃ 1 ፕሮጀክት ጉልህ የትራፊክ የአቅጣጫ ቅያሬ (ወይም አማራጭ መንገዶችን ለመውሰድ የሚመርጡ ሰዎች) ይኖራሉ ብለን አንጠብቅም።
ተጨማሪ ጉዞዎችን ወደ ሕዝብ መጓጓዣ መቀየር አስፈላጊ እንደሚሆን እናውቃለን:
- ብዙ ሰዎችን ይበልጥ አስተማማኝ ከሆነ የሕዝብ መጓጓዣ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይረዳል
- በአካባቢው ሰፈሮች ውስጥ የትራፊክ አቅጣጫ መቀየር ተጽእኖዎችን ለመቀነስ ያግዛል
የደረጃ 2 ፕሮጀክት ስናዳብር ሰዎች የሕዝብ መጓጓዣን ለመሳፈር እንቅፋቶችን እንዴት መፍታት እንደምንችል የበለጠ ለመረዳት በ2022 ተጨማሪ ማዳረስን እናደርጋለን። እንደዚያ የማዳረስ አካል፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ በተሻለ ለመረዳት በተጨማሪም ለማዳመጥ አቅደናል:
- የትራፊክ አቋርጦ-መዝለቅ ስጋቶችን ተስፋ ለማስቆረጥ እና ልንተገበር የምንችላቸው ሊሆኑ የሚችሉ ስልቶች
- ሰዎች መንዳት ሲያስፈልጋቸው መንገዶቹ ግልጽ ሆነው እንዲቆዩ፣ ብዙ ሰዎች የበለጠ ጉዞዎችን ወደ ሕዝብ መጓጓዣ እንዲቀይሩ ወይም በቀን መጨናነቅ ባነሰበት ጊዜ እንዲጓዙ ለመርዳት የሚያስችሉ ስልቶች
ብስክሌት ለሚጋልቡ ሰዎች Rainier Ave S ጠቃሚ መስመር ነው። ብስክሌት ለሚጋልቡ ሰዎች ሁኔታዎችን ለማሻሻል ምን ማሻሻያዎችን እያደረጉ ነው?
ብስክሌት ለሚጋልቡ ሰዎች Rainier Ave S ጠቃሚ መንገድ እንደሆነ ሰምተናል ምክንያቱም ብዙ ጊዜ እጅግ ጠፍጣፋ እና ቀጥተኛ መስመር ነው። Rainier Ave S ለሕዝብ መጓጓዣ፣ ለጭነት እና ለሌሎች ተሸከርካሪዎችም ደግሞ አስፈላጊ እና ብዙ ጊዜ የሚጠቀሙበት መስመር ነው። የመንገድ እና የሕዝብ መንገዶችን ቦታ መብት ውስንነት በተመለከተ የለውጦችን ውሳኔ በምንሰጥበት ጊዜ እነዚህን ፍላጎቶች እና ቅድሚያዎች የሚሰጣቸውን ነገሮች ማመጣጠን አለብን። እስከ ዛሬ ድረስ፣ ለRainier Ave S የማህበረሰቡ ሁለት ዋና ቅድሚያዎች ግጭቶችን መቀነስ እና አውቶቡሶች እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ መሆናቸውን ሰምተናል።
በዋሽንግተን ስቴት ህግ መሰረት ሰዎች በአውቶቡስ-ብቻ መስመሮች ብስክሌት እየጋለቡ እንዲጓዙ ይፈቀድላቸዋል። በኩርባ-ጎን አውቶቡስ መስመሮች ላይ ብስክሌት የሚጋልቡ ሰዎች አውቶቡሶች ብዙውን ጊዜ የመስመር-ውስጥ ማቆሚያዎችን እንደሚያደርጉ እና በጥንቃቄ እንዲጓዙ ማስታወስ አለባቸው። በስቴቱ ህግ መሰረት ማንም ከፊት ያለው ቅድሚያ ይኖረዋል።
በአሁኑ ጊዜ የብስክሌት መንገዶችን ለRainier Ave S የታቀደ ባይሆንም፣ በእግር፣ በብስክሌት እና በሚያንከባለሉ ሰዎች ላይ ሁኔታዎችን የሚያሻሽሉ ሌሎች ለውጦችን በRainier Ave S ላይ እያደረግን ነው። ከእነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ ብዙዎቹ የመስመር 7 ትራንዚት-ፕላስ መልቲ-ሞዳል ኮሪደር (Route 7 Transit-Plus Multi-Modal Corridor)ን ጨምሮ በአቅራቢያ ካሉ ፕሮጀክቶች ጋር እየተገነቡ ነው። የ2014 የቢስክሌት ማስተር ፕላን ከ Mt Baker Blvd በስተሰሜን Rainier Ave S ላይ የተጠበቁ የብስክሌት መንገዶችን እንዲኖሩ ሀሳብ ያቀርባል። ከደረጃ 2 ፕሮጀክት ጋር ወደ ሰሜን አቅጣጫ ያሉ የአውቶቡስ ብቻ መስመሮችን ለማስፋት አማራጮችን ስንገመግም፣ Rainier Ave S ላይ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ እና የሚጓዙ ሰዎች መንገዱን አሁን እንዴት እንደሚጠቀሙበት እና ሰዎች ወደፊት እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚፈልጉ መረዳት እንድንችል ተጨማሪ የፍለጋ መድረስ እናደርጋለን።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ Rainier Ave S ላይ እንደ ሬኒየር ጐዳና ማሻሻያዎች ፕሮጀክት አካል የፍጥነት ገደቡን ወደ 25 MPH መቀነስ፣ መሪ የእግረኛ ምልክቶችን መትከል እና ሌሎች የደህንነት እና የትራፊክ ማረጋጋት እርምጃዎችን መገንባትን ጨምሮ ሁኔታዎችን እና ደህንነትን ለማሻሻል በRainier Ave S ላይ ሌሎች ለውጦችን አድርገናል።
ብስክሌት ለሚጋልቡ ሰዎች ሌሎች በአቅራቢያ ባሉ መንገዶች ላይ ማሻሻያ አድርገናል ወይም እያደረግን ነው፣ እነዚህን ጨምሮ:
- Rainier Valley Neighborhood Greenway
- በMartin Luther King Jr Blvd S የተጠበቁ የብስክሌት መስመሮች
- የLake Washington Blvdን እንዴት የበለጠ ብስክሌት የሚጋለብበት ይደረጋል ላይ ግብአት መሰብሰብ
መርሀ-ግብር
- በ2022 በስተመጀመሪያ ላይ: ሙሉ ንድፍ እና ለደረጃ 1 ፕሮጀክት ማዳረስን መጨረስ
- ሐምሌ 2022: የደረጃ 1 ፕሮጀክት ግንባታ
- በጋ 2022: ላይ በደረጃ 2 ፕሮጀክት ላይ ግንዛቤን መጀመር
- 2023-2024: የደረጃ 2 ፕሮጀክት የመጨረሻ ንድፍ እና ትግበራ መጨረሻ
ደረጃ 1:
ደረጃ 2:
ተዛማጅ ፕሮጀክቶች
መስመር 7 ትራንዚት-ፕላስ ማልቲሞዳል ኮሪደር (Transit-Plus Multimodal Corridor)
የገንዘብ ድጋፍ
ይህ ፕሮጀክት በህዳር 2020 የሲያትል የሕዝብ መጓጓዣ መለኪያን (ለስምምነት የቀረበ ሃሳብ 1/Proposition 1) ላሳለፉት 80 በመቶው የሲያትል መራጮች ምስጋና ይግባውና ይህም በከተማችን ውስጥ በተደጋጋሚ፣ አስተማማኝ እና ተደራሽ የሆነ የአውቶቡስ አገልግሎት የገቢ ምንጭ ፈጠረ። በ0.15% የሽያጭ ታክስ (በ$100 ዶላር ግዢ ከ15 ሳንቲም ጋር የሚመጣጠን) በማህበረሰብዎ ውስጥ የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎትን በቀጥታ እየደገፉ ነው።
ቁሶች
የፕሮጀክት ቁሳቁሶች እንደዳበረ እዚህ ይጋራሉ።